Monday, March 17, 2014

ለበረከት ተጠርታችኃል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ታላቅ የምርቃት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን



በኢ/ኦ/ቤተክርስቲያን በሃዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በአንሌሞ ወረዳ የኤንጦ ላፍቶ ሌንቃ  መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ውስጥ ቤተክርስቲያናቸው በኢ-አማንያን ተቃጥሎባቸው ለ 36 ዓመታት በዛፍ ስር በመሰብሰብና ስዕለ  መድኃኔዓለም በማኖር ስርዓተ አምልኮ እየፈጸሙ ላሉት ምዕመናን የተጀመረውን ቤተክርስቲያን በፈቃደ እግዚአብሔር ከፍጻሜ ደርሶ ሚያዝያ 26 ቀን ይመረቃል፡፡ ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ሚያዝያ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ጉዞ አዘጋጅቶአል። በዚህም ጉዞ እርስዎም የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ መድኃኔዓለም ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መነሻ ቀን፡ ሚያዝያ 25 

መነሻ ሰዓት፡ ከቀኑ 8 ሰዓት

መነሻ ቦታ፡ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በእሳት አደጋ በኩል (ሰሜን በር)

የጉዞ ዋጋ፡ 250.00 ብር ከሙሉ መስተንግዶ ጋር

ለበለጠ መረጃ፡ 0911 53 41 97

                   0911 14 36 53

                   0930 10 05 81

                   0911 80 34 35

                  0911 92 18 30

                  0910 01 60 08

                  0911 16 96 68

ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

በመጀመርያ ይህን ሁሉ ላደረገ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው እንላለን!!
ለበረከት ተጠርታችኃል
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው። (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡10)
የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን እዚህ ደርሷል እልልልልልልልልል የቀረው የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች:- ምንጣፍ, የበረንዳ ግሪል, ጎረንዳዬ , ደውል, የመሬት ሸክላ(ቴራዞን) በረንዳ ዙሪያ ለማንጠፍ፤ በደንብ የተጠረበ ከድንጋይ የተሰራ ወለል ንጣፍ ቤተክርስቲያን ዙሪያ፡፡
ለዚህም የተቀደሰ አላማ እጃችሁን በመዘርጋት እንድትረዱና የበረከቱ ተካፋይች ትሆኑ ዘንድ መድሐኔዓለም ስም እንጠይቃለን፡፡
ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር Commercial Bank of Ethiopia, Bomb Tera Branch. Account no. 1000017080249 mobile +251911143653, +251911780816, +251910016008
ይህንን የምታዩትን ቤት Like በማድረግ እና ለሌሎችም እንዲያደርጉ በመጋበዝ እንዲሁም ይህንን የምታዩትን በመካፈልና በመርዳት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በመድኃኔዓለም ስም እንጠይቃለን።

ክብር ምስጋና ለመድሓኔአለም ይሁን፡ የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን ያብቃን፡