Showing posts with label ነገረ ቅዱሳን. Show all posts
Showing posts with label ነገረ ቅዱሳን. Show all posts

Sunday, January 13, 2013

ጥር 6



ከጌታችን እየሱስ ከርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱና የመጀመሪው ነው፤ ግዝረተ ክርስቶስ ይባላል፤ ሉቃ 1 21   “ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።  እመቤታችን ወደ ግዘረት ቤት ወሰደችው፤ ገራዡ ምላጩን ይዞ ቀረበ ነገር ግን ምላጩ እጁ ላይ ሳላ ውሃ ሆኖ ፈሰሰ፤ ጌታችንም በተአምራት የተገረዘ ሆኖ ተገኘ ይላል፤ ምነዋ ቢባል ጌታችን ደሙ የሚፈሰው ስጋውም  የሚቆረሰው አንዴ በእለተ ዐረብ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን የሰውን ስርዓት ሁሉ ጠብቋል፤ እራሱ እንደተናገረው  እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ማቴ 5 17 አምላክ ነኝና እለቱን ተጸንሼ እለቱን ልወለድ አላለም 9 ወር 5 ቀን ቆይቶ ተወለደ እንጂ እንደ ህጻናትም ዋይ ዋይ እያለም አለቀሰ፤ ደግሞም እየው በዛሬዋ ዕለትም ተገረዘ፤ የሚገርም ነው፡፡ መገረዝ ወይም አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው፤ ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነበር በአማናዊው ጥምቀት ተተክቷል፡፡ እርሱ የጥበበኞች ፈጣሪ ሲሆን  ፊደል ሊቆጥር ወደ  ቄስ ትምህርት ቤት የኔታ መምህሩ ጋር ሄዷል፤ መምህሩ አሌፍ በል አለው ጌታም አሌፍ አለ፤ አሌፍ ማለት የዕብራይስጥ ሆሄ ነው እኛ እንደምንለው እነሱ ደግሞ   አሌፍ ቤት ጋሜል  ዳሌጥ    ዋው  ዛይይላሉ፤ አናም ፊደል መቁጠር ጀመረ አሌፍ በል አለው አሌፍ አለ ቤት በል አለው መጀመሪያ የአሌፍን ትርጉም ንገረኝ እንጂ አለው መምህሩ ተናዶ እኔ የምልህን ዝም ብለክ በል አለው ጌታችንም መልሶ የአሌፍን ትርጉም ሳላውቅ ዘልዬ ቤት አልልም አለው ሂድ  ወላጅ ይዘህ አለው እመቤታችንን ይዞ ሄደ እኔ ልጅሽን ማስተማር አልችልም ይዘሽሊኝ ሂጂ አላት መምህሩ የአሌፍን ትርጉም ስለማያውቀው ነው፤ ማለት ሀለዎተ እግዚብሔር መሆኑን ስንቶች መምህራኖች ነግረውን ይሆን ለዚያም ነው እኮ “” ሀሌታዋ ”” የምንለው አጋ-ጣሚ ሆኖ ዛሬ የታላቁ አባት  የኖህ እረፍቱ ነው፤ “”ሐመሩ ”” የምንለው ስያሜውን ያገኘው ከዚሁ ከኖህ መርከብ ነው፤ ሐመር ማለት መርከብ ማለትም አይደል፡ ይህም የእመቤታችን አንድም የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፤ ጎበዝ መምህራን ፊደል ሲያስቆጥሩ ትርጉሙን ጭምር እየተናገሩ ታሪኩን እያነሱ እያወሱ ያስተምሩ ነበር፤ መምህር ግን ትርጉሙን አያውቅም ነበርና ጌታን ወላጅ አምጣ አለው፤ ልጅሽን ማስተማር አልችልም ከአቅሜ በላይ ነው አለ፤ ሰፊ ታሪኩ ታምረ እየሱስ ላይ ይገኛል፡፡ ሌላው በዛሬዋ ቀን ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደበት ቀን ነው፤ የዚህ ነብይ ልደቱ ታህሳስ 1 ቀን ነው፤  አዲስ አበባ አንጦጦ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ አለ ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ ከበዓሉ በረከት ያደሳትፈን፡፡   

                                ኤሊያስ በሰረገላ ወሰደው ደመና

                               ኤሊያስ ያረገው በእሳት ሰረገላ

                               በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ    

Wednesday, January 9, 2013

ጥር 1



እነሆ  የተባረከ ወርሃ ጥር ባተ፤ ይህ ወር ቀኑ 14 ሰዓት ሌሊቱ 10 ሰዓት ነው። በዚህ ወር ታላላቅ በዓላት ይከበራሉ ከነዚህም መካከል፤ብርሃነ ጥምቀቱ፤ ግዝረቱ፤ ቃና ዘገሊላ፤ ቅድስት ስላሴ፤ የእመቤታችን እረፍት፤የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽሙ፤ የዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤የነብዩ ኤልያስ፤የቅዱስ ኡራኤል ዓመታዊ በዓላቸው ሲሆኑ ሌሎችም ታላላቅ ቅዱስን አባቶች ታስበውና ተዘክረው ይውላሉ። እነሆ ጥር 1 ቀን የቀዳሚ ሰማዕት የሊቀ ዲያቆናት የቅዱስ እስጢፋኖስ የእረፍት ቀኑ ነው፤ የዚህ ሰማዕት ልደቱም በዚሁ ቀን ነው። በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ ዝነኛው ገዳሙ ሃይቅ እስጢፋኖስ በመዲናችን አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚገኘው ደብሩ ከቀደምቶቹ አንዱ ነው። እስጢፋኖስ ማለት ወደብ ጸጥታ ማለት ሲሆን ቁጥሩ 72 አርድዕት ነው፤ ለምን ቀዳሚ ሰማዕት ተባለ ከሱ በፊት ሰማዕታት የሉም ነበርን ? ቢሉ መኖርስ አሉ የእርሱ ግን ቀዳሚ መባሉ ከጌታችን እርገት በኃላ ስለ ጌታችን መውረድ መወለድ መስክሮ የሞተ የመጀመሪያው እርሱ ስለሆነ ነው፤ እሺ ለምንስ ሊቀ ዲያቆናት ተባለ ቢሉ በሐዋርያት እጅ ከተሾሙት ሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የሁሉም አለቃ እርሱ ስለሆነ ነው ሐዋ 6 5 መጽሐፍ ቅዱስ ስለእስጢፋኖስ እንዲህ ሲል በእውነት መሰከረ "እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበረ...ፊቱም የመልአክ ፊት ይመስል ነበር   ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ  አልቻሉም ሐዋ 6 8 እህሳ  አይሀድ አማጽያን መልስ መስጠት ቢያቅታቸው ድንጋይ አነሱ ልብ አናቱን እያሉ ወገሩት፤  ቀና ብሎ ቢመለከት ቅድስት ስላሴን አየ፤ አቤቱ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው ይቅር በላቸው እያለ  ነፍሱን ሰጠ። ሐዋ 7 60

ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው በኢየሩሳሌም በምትገኝ ሐኖስ በተባለች ቦታ ነው:: አባቱ ስምዖን ሲባል እናቱ ደግሞ ሐና ትባላለች ነገዱ ከነገደ ብንያም ነው :: የኦሪትን ሕግና ሥርዓት ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ተምሯል::በሐዋርያት ሥራ ምዕ. 6 እንደምናነበው ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ( ሊቀ ዲያቆን) ሆኖ ተሹሟል ይህም የሆነው በጥቅምት 17 ነው ::
ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ተአምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደክርስትና መልሷል:: በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን (እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ) ተመለከተ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ "ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው "በመጨረሻም "ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" ብሎ ነፍሱን ሰጠ ::የሐዋርያት ሥራ ምዕ 7
በተወለደ 30 ዓመቱ 35 . በሰማዕትነት ዐረፈ::

ከሰማዕቱ በረከት ያሳትፈን።  

Thursday, December 13, 2012

ታህሳስ 5



በዚህች ቀን ቅድስት አውጋንያ አረፈች፤ አገሯ እስክንድርያ ነው አባቷ አገር ገዢ ነበር ፊሊጶስ ይባላል ጣኦት አምላኪ ነው እናቷ ግን ደግ ክርስቲያን ነበረች በድብቅ ክርስትናን አስተማረቻት ስታድግ ታላላቅ መኳንንቶች አጯት እርሷ ግን ጠፍታ ወደ አባ ቴዎድሮስ ገዳም ገባች መነኮሰች ማንም ሰው እንዳያውቃት ፍጹም ወንድ መሰለች ስሟንም አባ አውጋንዮስ አሰኘች፤ አባቷ ጠፍታ መቅረቷን ባወቀ ጊዜ መሪር ለቅሶ አለቀሰ እሷን የሚመስል ጣኦት አስቀርጾ ማምለክ ጀመረ። ከአንድ ዓመት በኃላ ትጋቷን አይተው መነኮሳቱ የገዳሙ አበምኔት አድርገው ሾሟት፤ (አበምኔት ለወንድ እንደሆነ ልብ ይሏል) እግዚያብሔር በሰይጣና...ትና በድውያን ላይ ፍጹም ስልጣን ሰጣት ከብዙ አገር በሽተኞች እየመጡ በእጇ ይፈወሱ ነበር፤ ከእለታት አንደ ቀን ግን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት ቅድስት አውጋንያን ባየቻት ጊዜ ወንድ መስላት ፍጹም ወደደቻት፤ ምንኩስናህን ትተህ ባል ሆነከኝ ከኔ ጋር ኑር አለቻት፤ ሂድ አንተ ሰይጣን ብላ አባረረቻት፤ ባሳፈረቻት ጊዜ ወደ አገር ገዢው ሄዳ በዚያ ገዳም የሚኖር መነኩሴ ሊደፍረኝ ሲል አምልጬ መጣሁኝ አለችው፤ ዘፍጥረት 39 14 መኮንኑ በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሁሉንም መነኮሳት ታስረው እንዲሰቃዩም አደረገ፤ የሞቱም አሉ፤ ቅድስት አውጋንያ ስቃያቸውን ባየች ጊዜ መኮንኑን ጌታዬ እውነቱን እነግርሃለው የምፈልገውን ነገር ግን አትከልክለኝ አለችው፤ አስማለችውም፤ ከዚያም ልጁ አውጋንያ እንደሆነች ገለጸችለት፤ አንገቷን አቅፎ አለቀሰ፤ እኔም ባንቺ አምላክ አምናለው አላት ከነቤተሰቦቹም ተጠመቀ የበቃ ታላቅ አባት እስከመሆን ደርሶ በሰማእትነት ነው የሞተው እርሷም ወደ ሮም ሄዳ የገዳም እመምኔት ሆና ለብዙ ዘመናት ለረጅም ወራት በተጋድሎ ኖራ ታህሳስ በባተ በአምስተኛው ቀን አረፈች፤ በረከቷ ይደርብን ከጻድቁ አቡዬ በረከታቸውንም ያሳትፈን።