Monday, March 17, 2014

ለበረከት ተጠርታችኃል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ታላቅ የምርቃት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ላፍቶ ሌንቃ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን



በኢ/ኦ/ቤተክርስቲያን በሃዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በአንሌሞ ወረዳ የኤንጦ ላፍቶ ሌንቃ  መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ውስጥ ቤተክርስቲያናቸው በኢ-አማንያን ተቃጥሎባቸው ለ 36 ዓመታት በዛፍ ስር በመሰብሰብና ስዕለ  መድኃኔዓለም በማኖር ስርዓተ አምልኮ እየፈጸሙ ላሉት ምዕመናን የተጀመረውን ቤተክርስቲያን በፈቃደ እግዚአብሔር ከፍጻሜ ደርሶ ሚያዝያ 26 ቀን ይመረቃል፡፡ ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ሚያዝያ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ጉዞ አዘጋጅቶአል። በዚህም ጉዞ እርስዎም የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ መድኃኔዓለም ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መነሻ ቀን፡ ሚያዝያ 25 

መነሻ ሰዓት፡ ከቀኑ 8 ሰዓት

መነሻ ቦታ፡ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በእሳት አደጋ በኩል (ሰሜን በር)

የጉዞ ዋጋ፡ 250.00 ብር ከሙሉ መስተንግዶ ጋር

ለበለጠ መረጃ፡ 0911 53 41 97

                   0911 14 36 53

                   0930 10 05 81

                   0911 80 34 35

                  0911 92 18 30

                  0910 01 60 08

                  0911 16 96 68

No comments:

Post a Comment