Friday, January 23, 2015

የተጀመረውን ቤተክርስቲያን በፈቃደ እግዚአብሔር ከፍጻሜ ደርሶ ሚያዝያ 26 ቀን ተመረቀ

የተጀመረውን ቤተክርስቲያን በፈቃደ እግዚአብሔር ከፍጻሜ ደርሶ ሚያዝያ 26 ቀን ተመረቀ፡፡ ቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት 35 ዓመታት በዛፍ ስር ጤዛ ላይ መንበርከክ ያለ አስተማሪ መጽናት በአህዛብ መካከል ክርስትናን መግለጥ ምን ይህል ታላቅ ነው!!!!!

“የሰማይአምላክያከናውንልናል፥እኛምባሪያዎቹተነሥተንእንሠራለን” ነህ.2፡20

በመጀመሪያ ይህን ሁሉ ላደረገ ለዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው፡፡ የቅዱስ እንጦንስ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር በሃዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በአንሌሞ ወረዳ በኤንጦ የምትገኘው ላፍቶ ሌንቃ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ደስ በሚል እና ልብ በሚነካ ሁኔታ ቤተክርስቲያንዋ ሚያዝያ 26 ቀን ተመርቃለች፡፡እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ ለኦርቶዶክስ ምእመናን አገልግሎት መሰጠት ጀምራለች ለሁሉም ኦርቶዶክስ ምእመናን እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ቤተክርስቲያኗ ተጀምራ ለፍፃሜ እስክትበቃ ድረስ በፀሎት፣በገንዘብ፣በቁሳቁስ እና በሃሳብ ለረዳችሁን ክርስቲያኖች በሙሉ ማህበሩ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል፡፡በመቀጠልም ቤተክርስቲያንዋ እራስዋን የምትችልበት ሁኔታ ማመቻቸት እና የተሟላ አገልግሎት እንድትሰጥ ለማድረግ ማኅበሩ የተለያዩ እንቀስቃሴዎችን ለማድረግ አቅዷል፤
• የአጭር ግዜ እቅድ ቤተክርስቲያኗ ሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደትችል የካህናት ደሞዝ እና አስተዳደራዊ ወጪዎችን ከምእመኑ ማሰባሰብ፡፡
• የረዥም ግዜ እቅድ ቤተክርስቲያኗ በተሰጣት ቦታ ላይ እና በአካበቢዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት በራሷ ገቢ እንድትተዳደር ማድረግ ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት የአጭር እና የረዥም ግዜ እቅድ ለማሳካት በቅርብም በሩቅም ላላችሁ የማህበሩ አባላት እና ምእመናን በመድኃኔዓለም ስም እጃችሁን እንድትዘረጉ እና የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የባንክ አካውንት ቁጥር 1000017080249 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርካቶ፤ቦንብ ተራ ቅርንጫፍ ፡፡
ለተጨማሪመረጃ በእነዚህ ስልክ ይደውሉ
+251911 14 36 53
+251911 24 90 37
+251930 10 05 81
+251910 01 60 08
ወስብሐትለእግዚአብሔርወለወላዲቱድንግልወለመስቀሉክቡርአሜን !
‹‹የጠራችሁአምላክ የታመነ ነው ››1ኛተሰ 5፡14

No comments:

Post a Comment